“አልተውሽም”
የልጅነት ፍቅሬ
የተስፋዬ ፍሬ
የእድሜ ልክ ማገሬ
አልተውሽም ፍቅሬ
ከሜዳ ላይ ጥዬሽ
እንዲበላሽ አውሬ
አላደርግም ማሬ
አንቺ ማለት ለኔ…………..
የልጅነት ውበት
የድካሜ ብርታት
የናፍቆቴ ጥማት
…….ባለቤቴ እኮ ነሽ……..
አልተውሽም ፍቅሬ
አንቺን ይዤ ስሄድ………..
ተራራው ሜዳ ነው
ፀሀዩ ብርታት ነው
እርጅናው ምርኩዝ ነው
አንቺን ከተውኩ ግን…….
ሜዳውም ይሆናል ተራራ
እኔም እደክማለው በፀሀይ ጠራራ
እርጅናውም ቢሆን ሬት ነው መራራ
አልተውሽም ፍቅሬ………
የጥንቱ ቃላችን ላልተውሽ ላተይኝ
የተማማልንበት መቼ ተዘነጋኝ
ልክ እጅሽን ስይዝ……….
ብርሀን ይታየኛል
ጉልበት ይኖረኛል
ማርጀቴ ይጠፋኛል
….እናም አልተውሽም…….
ገላችን ቢያረጅም
ፍቅር አያረጅም
አንቺም እንዳተይኝ
እኔም አልተውሽም
በቃ….አልተውሽም